ብስክሌት መንዳት የወንዶች የመራቢያ አካልና ኩላሊት ላይ ጉዳት እንደሌለው አንድ ጥናት ጠቆመ

ብስክሌት  መንዳት የወንዶችን  የመራቢያ አካል ወይም የኩላሊትን  ሥራ እንደማያስተጓጉል አንድ ጥናት  ጠቆመ ።

ተመራማሪዎች  ከሩጫና ከዋና ጋር  በማነጻጻር  ብስክሌት መንዳት ምን ያህል  በወንዶች መራቢያና የኩላሊት  የዕለት ተዕለት ተግባር  ተፅዕኖ እንዳለው  ጥልቀት   ያለው  ጥናት  አድርገዋል ።    

ከዚህ ቀደም የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ብስክሌት መንዳት በወንዶች  የመራቢያ አካል ላይ  የረጅም ጊዜ  ጉዳት  እንዳለው ሲገልጹ  የቆዩ  ቢሆንም   የዚህ   ጥናት  ውጤት  እንደሚያመለክተው  ግን  ብስክሌት  መንዳት ከሚኖረው ጉዳት ይልቅ  ባርካታ ጥቅሞች እንዳሉት አረጋግጧል  ።

እንደ ተመራማሪዎቹ  ገለጻ ብስክሌት መንዳት  በካንሰር የመያዝ  ዕድልን በግማሽ ይቀንሳል በሚል  አስገራሚ የጥናት ውጤት ይዘው ብቅ ብለዋል ።   

ጥናቱ  2ሺህ 774 የሚደርሱ  ከእንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ካናዳ ፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ብስክሌት የሚነዱ  ወንዶችን በማካተት የተሠራ  ሲሆን  ለንጽጽር እንዲሆን   539 ዋናተኞች ፣ 789 ሯጮች  በጥናቱ  ተካተዋል  ።  

በጥናቱ  ውጤት መሠረት ብስክሌት  መንዳት በወንዶች የልብ ጡንጫና በመገጣጠሚያ የሰውነት ክፍሎች ላይ  ትልቅ ጠቀሜታ  እንዳለው  የተመራማሪዎቹ  አስተባባሪ ቤኒያሚን ብሬየር ይናገራሉ ።

እንደ  ቤኒያሚን ገለጻ ብስክሌት መንዳት ለጉዳት ይልቅ  በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት  ለማረጋገጥ ችለናል ብለዋል ።

ብስክሌት የሚነዱ ወንዶች የመራቢያ አካላቶቻቸው ኩላሊቶቻቸውም የተለመደውን መገበኛ ተግባር በጥሩ ሁኔታ  የሚፈጽም እንደሆነ አይተናል ብለዋል አጥኚዎቹ።