የአዋላጅ ነርሶች ቁጥር ማነስ ለአገልግሎት ጥራት ማነስ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ሚድዋይፈሮች ማህበር አስታወቀ ።
የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የአዋላጅ ነርስ ባለሙያዎች አስፈላጊነት ከፍተኛ መሆኑን የሚጠቅሱት ባለሙያዎች አሁን እየታየ ያለው የአዋላጅ ነርስ ቁጥር ማነስ ለአገልግሎት ጥራት ችግር እየሆነ መምጣቱን ማህበሩ ገልጿል ።
በአሁኑ ወቅት ከአገሪቱ ህዝብ ቁጥር አኳያ ከቅድመ ወሊድ ጀምሮ ሰባት አይነት ክህሎት ያላቸው አዋላጅ ነርሶችን ቁጥር ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋርም መሥራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል ።
ኢትዮጵያ አሁን ያላት የአዋላጅ ነርስ ባለሙያዎች ቁጥር ከአስራ ሁለት ሺ የማይበልጡ መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች የሚገልጹ በአሁኑ ወቅት ግን አገሪቷ ሀምሳ ሺ የሚሆኑ የአዋላጅ ነርሶች እንደሚያስፈልጋት የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ ፡፡