የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት በአዲስ አበባ የድሃ ድሃ የሚባሉትን ወይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዳይገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በአመት 300 ብር የአባልነት ክፍያን ብቻ በመክፍል ነው ዓመቱን ሙሉ ገደብ የሌለው የጤና አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ዋልታ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል ።
የህክምና አገልግሎቱ ከሚሰጡባቸው በአንዱ የልደታ ከፍለ ከተማ በመገኘትም የሚመለከታቸውን አካላት በማናገር በዚው ጉዳይ ተጨማሪ ዘገባ ብርሃኑ ወልደሰማያት አዘጋጅቷል ።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በበኩሉ የጤና አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው ባለመብቶች ሁሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይበልጥ ሥራ እየተሠራ መሆኑን አመልክቷል ።