በ3 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጭ የተገነባው ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች ማስወገጃ ማዕከል ስራ ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ

በ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ወጭ የተገነባው ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማስወገጃ ማዕከል ስራ ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአዳማ ከተማ በ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ወጭ የተገነባው ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች ማቃጠያ ዘመናዊ ማዕከል ከ2 ሳምንት በኋላ ስራ አንደሚጀምር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ማዕከሉን በጎበኙቱበት ወቅት እንደገለጹት ማዕከሉ ጊዜያቸው ካለፈባቸው መድኃኒቶች አወጋገድ ጋር ተያይዞ ከህብረተሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት ያስችላል።

ማዕከሉ ጊዜያቸው ያለፋባቸው መድኃኒቶችን በማስወገድ አቅምና ጥራት በአፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን፥ በሰዓት 1 ሺህ ኪሎ ግራም ጊዜ ያለፈባቸውን መድሀኒቶች ማቃጠል የሚችል ነው ተብሏል።

በሌሎች 7 ቦታዎች ተመሳሳይ ማዕከላት እየተገነቡ ሲሆን፥ ከ3 ወር በኋላ ወደ ስራ እንደሚገቡ ታውቋል።

ይህን ማዕከል ጨምሮ በግንባታ ላይ ለሚገኙት ማዕከላት ከ13 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጭ መደረጉም ተነግሯል። (ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ)