የሴቶች ልማት ቡድን ብቃት ማጎልበቻ ስልጠናን ወስደው ላጠናቀቁ እውቅና ተሰጣቸው

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አድአ ወረዳ የሴቶች ልማት ቡድን ብቃት ማጎልበቻ ስልጠናን ወስደው ላጠናቀቁ እውቅና ተሰጣቸው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አድአ ወረዳ በአገር አቀፍ ደረጃ ሁሉንም የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ በመተግበር ሞዴል ቤተሰብ ከሆኑ እማወራዎች 37 የሚሆኑት መደበኛ የ52 ሰአት ስልጠና በመውሰድና የደረጃ ብቃት ምዘና ፈተና በማለፍ የደረጃ አንድ ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል::

ይህ ስልጠና ሞዴል የሆኑት ቤተሰቦች ዘለቄታ ባለው መንገድ እንዲቀጥሉ የሚረዳና አንድ እማወራን የጤና ኤክስቴንሽን ደረጃ ሊያደርስ የሚችል ነው::

በአሁኑ ጊዜ 81 ሺህ 500 እማወራዎች ስልጠና ላይ ሲሆኑ በዚህ አመት መጨረሻ 1ሚሊዮን ለሚሆኑ እማወራዎች ስልጠናው ይሰጣቸዋል፡፡

ወ/ሮ ንጋቷ ሙሉጌታ እና ወ/ሮ ገነት ጃርሶ የአድአ ወረዳ ነዋሪ ናቸው ፡፡ በደረጃ አንድ የጤና የኤክስቴንሽን ፓኬጅ ስክጠና ወስደው እና ፈተናውን አልፈው ማረጋገጫ ወስደዋል፡፡

እነዚህ ሁለት እማወራዎች እንደተናገሩትም ስልጠናው የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ጤና ለመጠበቅ  የሚያግዛቸው መሰረታዊ የጤና አጠባበቅ ትምህርት መውሰዳቸውን ይናገራሉ፡፡

በዚህም የግልና የአካባቢ ንጽህና እንዲጠብቁ፣ መጸዳጃ እንዲያዘጋጁ፣ ምግባችን አመጣጥነው እንዲያዘጋጁ ፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙ እና መሰል ጤንነታቸው ለመጠበቅ የሚያስችላቸው ተግባራትን እንዲያከናውኑ እንደረዳቸው ይመሰክራሉ፡፡

በቀጣይ ከራሳቸው አልፈው ስልጠናውን ላልወሰዱ ጎረቤቶቻቸው ትምህርቱን እንደሚያካፍሉ የተናገሩት ሰልጣኞቹ መሰል ስልጠናዎች በመንግስት በኩል ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል::/የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር/