በሳዑዲ ዓረቢያ የነበሩ 600 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በህገ ወጥ መንገድ ይኖሩ የነበሩ 600 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ።

በሳዑዲ ዓረቢያ ጂዛን አካባቢ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 600 ኢትዮጵያውያን በዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል ።

ኢትጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው የተመለሱትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጂዳ ከሚገኘው የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ፣ከሚመለከተው የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት እና ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።

መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ እና በተለያዩ ሀገሮች ችግር ያጋጠማቸውን ዜጎች ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለመመለስ በየሀገራቱ ከሚገኙ ኤምባሲዎችና ከአይ ኦ ኤም ጋር በመተባበር መብታቸው ተጠብቆና ተከብሮ በሰላም ወደ ሀገራቸው የመመለሱን ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ነው የተገለፀው።  (ምንጭ፡- የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)