በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል የ30ኛ ዓመት ምስረታ በዓል እያከበረ ነዉ

በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል የ30ኛ ዓመት ምስረታ በዓል እያከበረ ነዉ፡፡

መርጃ ማእከሉ “ስለልብ ብላችሁ፤ ከልብ አድምጡን” በሚል መሪ ቃል በዛሬዉ እለት ለ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እያከበረ ይገኛል፡፡

የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል ስራ አስኪያጅ አቶ ህሩይ አሊ በሰጡት መግለጫ ክብረ በዓሉ በተለያዩ ፕሮግራሞች ከሰኔ 1 እስከ 8 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ በልብ ህመም ምክንያት የሚሰቃዩ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የጥናት ዉጤት እንደሚያሳየዉ ማዕከሉ ተመላላሽ ህመምተኛን ሳይጨምር በ30 አመት ዉስጥ ከ7 ሺህ 800 በላይ ህፃናት እና አዋቂዎች የልብ ቀዶ ጥገና ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪ በሀገር ዉስጥ በ10 ዓመታት ዉስጥ ከ4 ሺህ በላይ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል፡፡

የዝግጅቱ ዋና አላማም በዉጭ ሀገር እና ሀገር ዉስጥ ያሉት አካላትና ተቋማት እንዲሳተፉ ጥሪ ለማቅረብ ያለመ ነዉ ተብሏል፡፡