የወባ ትንኞችን 99 በመቶ የሚገድል ፈንገስ ተገኘ

ዘረ መሉ የተቀየረ ፈንገስ የወባ ትንኞችን 99 በመቶ በፍጥነት እንደሚገድል አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማምረት ተብሎ ዘረ መሉ በቤተ ሙከራ የተሻሻለው ፈንገስ የወባ በሽታን የሚያስተላልፉ ትንኞች በፍጥነት ሲገድል እንደታየ ነው በጥናቱ የተገለፀው።

ዝርያው በአውስትራሊያ ከሚገኝ መርዛማ ሸረሪት የተቀመመውን መርዛማ ንጥረ ነገር በቤተ ሙከራ ከፈንገሱ ዘረ መል ጋር በማጣመር የተሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

በቡርኪና ፋሶ የተካሄደው ሙከራ እንደሚያሳየው በ45 ቀናት ውስጥ 99 ከመቶ የሚሆኑ የወባ ትንኞች እንደሞቱ አሳይቷል።

ተመራማሪዎቹ ግን ዓላማቸው ነፍሳቱን ማጥፋት ሳይሆን የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት እንደሆነ ነው የገለፁት።

ሴቷ ትንኝ የሰው ደም በመምጠጥ በምታስተላልፈው የወባ በሽታ በየዓመቱ ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ይሞታሉ።

በመላው ዓለም በየዓመቱ 219 ሚሊዮን የሚጠጉ የወባ በሽታዎች ይከሰታሉ።

በዩናይትድ ስቴትስ የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችና በቡርኪና ፋሶ የሚገኘው የአር.ኤስ.ኤስ ምርምር ተቋም በመጀመሪያ ሜታርሂዚየም ፒንግሃንሴ የተባለ ፈንገስ እንደታወቀና ይህም በተፈጥሮው የወባ በሽታን የሚያስፋፉ አኖፌሌስ ሞስኪቶዎችን እንደሚጎዳ ነው የተረጋገጠው።

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)