በአገር አቀፍ ደረጃ ለማሟላት ከታቀደው 500 የላቦራቶሪ ማሽኖች ውስጥ የ50ዎቹ ተከላ ተከናወነ

በአገር አቀፍ ደረጃ 500 የጤና ተቋማትን በአዳዲስ የላቦራቶሪ ማሽኖች በሶስት አመት የማዕቀፍ ግዢ ለማሟላት በተያዘው እቅድ መሰረት የመጀመሪያዎቹ 50 ተቋማት ላይ ማሽኖቹ ተተክለው  ተመርቀዋል፡፡

ማሽኖቹ ከዚህ ቀደም በላብራቶሪ አገልግሎት ላይ የሚታዩ የኬሚካል አቅርቦት መቆራረጦችና የብልሽት ችግሮችን እንደሚፈቱና መገልገያ ቁሳቁሶቹ ከተለያዩ አለም አቀፍ የላብራቶሪ መገልገያ ማሽኖች አቅራቢ ድርጅቶች ስምምነት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ሶስት አመታትም ያለምንም መቆራረጥ ኬሚካሎችን የማቅረብና የጥገና አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

የማዕቀፍ ግዢ ስምምነቱ አቅራቢ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ የማሽኑን ግዥ እና የጥገና ወጪ የሚሸፍኑ ሲሆን የጤና ሚኒስቴር የላቦራቶሪ ኬሚካሎችን ወጪ የሚሸፍን ይሆናል::

እነዚህ ማሽኖች ዘመናዊና በሰአት እስከ 1600 ምርመራዎችን የማካሄድ አቅም ያላቸው ናቸው::/የጤና ሚኒስቴር/