አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ለኢትዮጵያ የልብ ማዕከል 1 ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገባ

አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል አንድ ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገብቷል፡፡

በዛሬው ዕለት ማዕከሉን የጎበኘው አትሌት ኃይሌ በጉብኝቱ ወቅት የተለያዩ የሕክምና ክፍሎችን እና የሥራ ቦታዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

አትሌት ኃይሌ ከጉብኝቱ በኋላ ማዕከሉን ለማጠናከር የሚውል የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግሯል። (ምንጭ፡-ኢቲቪ)