ደቡብ ሱዳን ለአስከፊ የምግብ እጥረት እየተጋለጠች መሆኑን ፋኦ ገለጸ

ባልተረጋጋ ፖሊቲካ ውስጥ ያለችው ደቡብ ሱዳን ለአስከፊ የምግብ እጥረት እየተጋለጠች መሆኑን በመንግስታቱ ድርጅት የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ገለጸ።

ድርጅቱ እንዳለው አሁን ላይ በሀገሪቱ አምስት ሚሊየን ዜጎች ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።

የፖሊቲካ ቀውሱ የሚቀጥል ከሆነም ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ዜጎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጿል።

በቅርቡ በመንግስትና ተቃዋሚዎች መካከል በተከሰተው ግጭት 30 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ የእርዳታ ምግብ መዘረፉን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅትም የሀገሪቱ የምግብ ዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። (ኤፍ ቢ ሲ)