የ2017 የበየነ መረብ ደህንነት ጉባኤ በቻይና እየተካሄደ እንደሆነ ተገለፀ

የ2017 የበየነ  መረብ ደህንነት ወይም የኤንተርኔት  ደህንነት ጉባኤ  በቻይና ቤጂንግ ከተማ  እየተካሄደ መሆኑ ተመለከተ ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ሀገራት እና የዓለማችን ትልልቅ ድርጅቶች የሳይበር ጥቃት እየተፈፀመባቸው ይገኛል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የተለያዩ መረጃዎች ሳይቀሩ በዚሁ ምክንያት የአደባባይ ሚስጥር ሆነዋል፡፡

በዚህም የሀገራት ትላልቅ ድርጅቶች ስጋት ውስጥ መሆናቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ተነግሯል፡፡

ይህ ችግር እራሰ ምታት የሆነባቸው የቴክኖሎጅ ተቋማት በቻይናዋ ከተማ ቢጂንግ የሳይበር ደህንነት ጉባኤ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በጉባኤው ላይ በዋነኝነት የተነሳው ስለ አዳዲሰ ቴክኖሎጂዎች ሳይሆን እንዴት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው የመረጃ ደህንንትን መጠበቅ እንደሚችሉ ነውም ተብሏል፡፡

ከድርጅቶችም ባለፈ ግለሰቦች የሚጠቀሟቸውን ድህረ ገፆችን ሳይቀር የሚበረብሩት የመረጃ ጠላፊዎችን ማስቆም እና የሳበር ደህንነትን ይበልጥ አሰተማማኝ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናገረዋል፡፡

የመረጃ ጠላፊዎችን  ለማስቆምም ሆነ የተለያዩ የየደህንነት መተግበሪያዎችን ለመጠቀም በርካታ መዋለ ንዋይ ማፈሰስ እንደሚገባም በጉባኤው ላይ የተገኙ የመረጃ ደህነነት ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡

በአለም ላይ ከ3 ቢሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የተለያዩ ድህረ ገፆች ተጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል፡፡

አብዛኛዎች ተጠቃሚዎች የሳይበር ደህነነት ጥቅምን እምብዛም ያልተገነዘቡ ናቸው በመሆኑም እዚህ ላይ ቅድሚያ መሰራት ይገባናል ያሉት በጉባኤው ላይ የተገኙት የጀርመን የመረጃ ደህነነት ፍባለሞያ የሆኑት ቢንጃሚን ኩንዝ ሚጅ ናቸው፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው እራሱን ለመከላከል ሲል በዚህ ዙሪያ መማር እና ክህሎቱን ማሳደግ ይገባዋልም ተብሏል፡፡

በዚህ ኮንፈረንስ ላይ በአለም ላይ የሚገኙ በመረጃ ደህንነት ዙሪያ ጥናት ያደረጉ እና በጉዳዩ ልምድ ያላቸው ባለሞያዎች ልምዳቸውን ያጋሩ ሲሆን መፍትሄ ያሏቸውን ጉዳዮችንም አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም በጉባኤው ላይ የመረጃ ደህንነትን በተመለከተ አዳዲሰ ህጎችም ፀድቀዋል ነው የተባለው፡፡(ምንጭ: ቢቢሲ)