የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቡራዩ ልዩ የተሰጥኦ ትምህርት ቤት እያስገነባ ነው

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቡራዩ ከተማ  በ708 ሚሊዮን ብር ወጪ  የልዩ ተሰጥኦ ትምህርት ቤት እያስገነባ መሆኑን ገልጿል፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተርር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የአካባቢው ማህበረሰብ ፕሮጀክቱን በየኔነት ስሜት እንዲደግፈው እና እንዲጠብቀው አደራ ብለዋል፡፡

በአካባቢው የሚገነባው ትምህርት ቤት በአገሪቱ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች የሚማሩበትና ጥሩ አስተሳሰብ ይዘው እንዲያድጉ የሚደረግበት እንደሆነም ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ  አገሪቱን ሊያስጠሩ የሚችሉ ፤በዓለም ላይ ተወዳደሪ የሆኑና እውቀት ያላቸው እንዲሁም የተለያዩ የግኝት ስራዎችን የሚሰሩ ተማሪዎች የሚፈሩበት እንደሚሆንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

የከተማ ነዋሪውም አሁን እየደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በማጠናከር ለትምህርት ቤቱ ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግ  ጥሪ አቅርበዋል።

መንግስት በ708 ሚሊዮን ብር እያስገነባ ያለው ይህ ትምህርት ቤት ግንባታው በዚህ ዓመት የተጀመረ ሲሆን በአንድ ዓመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።/ኢዜአ/