አካዳሚው በሌሰር ፊዚክስ ስኬታማ የፈጠራ ሥራ ላበረከቱት ሶስት ሳይንቲስቶች የኖቤል ሽልማት አበረከተ

 የስዊዲኑ ሮያል የሳይንስ አካዳሚ በፊዚክስ ዘርፍ በተለይም በሌሰር ፊዚክስ ስኬታማ የፈጠራ ስራዎች ላበረከቱ ሶስት ሳይንቲስቶች የኖቤል ሽልማትን አበርክቷል፡፡

ሽልማቱን ያሸነፉት አሜሪካዊው አርተር አሽኪን ፤ ፈረንሳያዊው ጄራርድ ሞውሮ እና ካናዳዊቷ ዶና ስትሪችላንድ ናቸው፡፡ አሜሪካዊው ሳይንቲስት አርተር አሽኪን  አንድ መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር የተሸለመ ሲሆን ፈረንሳያዊው እና ካናዳዊቷ ሳይንቲስቶች ደግሞ እያንዳንዳቸው ሀምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሸልመዋል፡፡

የሌሰር ፊዚክስ የጨረር ልቀትን በማነሳሳት ብርሃን ማጉላት የሚያስችል የፊዚክስ ዘርፍ ሲሆን ሌዘር ደግሞ ከፍተኛ የብርሃን ጨረር የሚያወጣ መሳሪያ ነው፡፡

ሳይንቲስቶቹ ሽልማቱን የተቀዳጁት በዚሁ መስክ ባከናወኗቸው ውጤታማ የፈጠራ ስራዎች ነው፡፡

ካናዳዊቷ ሳይንቲስት በታሪክ የፊዚክስ ሽልማትን የተቀበለች ሶስተኛዋ ሴት ሆና መመዝገቧን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡