“በሬ ለምኔ” የተሰኘው ዘመናዊ ማረሻ ወደ ስራ ሊገባ ነው

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዲዛይን ተደርጎ የተሰራውና በእጅ የሚገፋ "በሬ ለምኔ" የተሰኘው ዘመናዊ ማረሻ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂው የአርሶ አደሮችን ድካም በመቀነስ እርሻቸውን ከማቀላጠፉ በተጨማሪ ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ በሬዎችን በማድለብ እና ለስጋ ምርት ገበያ በማቅረብ ገቢያቸው እንዲጨምር ያግዛል ተብሏል።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱና ኑሯቸውን የሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ፈጠራና ማላመድ ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አድሱ "በሬ ለምኔ" የተሰኘው ቴክኖሎጂ በሚኒስቴሩ የስራ ኃላፊዎች ተጎብኝተዋል፡፡ (ምንጭ፦ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)