በአገሪቱ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕቅዶች አፈጻጻም ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል

ባለፈው የበጀት  ዓመት በአገሪቱ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት የተያዙት ዓመታዊ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕቅዶች በተወሰነ መልኩ እንዳይፈጸሙ ማድረጉን  ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተናገሩ ።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ በዛሬው ዕለት የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ  የመክፈቻ  ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በ2010  የአገሪቱ  ሁኔታ ሲታይ በአይነቱ  የተለየ መሆኑንና   በአገሪቱ  የተያዙት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ  ዕቅዶች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሠረት  እንዳይፈጸሙ አድርጓል ብለዋል ።

መንግሥት አገራዊ  መግባባት  ለመፍጠር ብቻውን ሲዳክር  እንደነበር  የጠቆሙት  ፕሬዚዳንቱ   ገዠው ፓርቲ ኢህአዴግ ዝርዝር ግምገማ  በማድረግ ተገቢውን  የአመራር ለውጥ በማድረግ ጭምር ባለፈው በጀት ዓመት በአገሪቱ  ዳግም የተስፋ ጎህ አንዲቀድ ሆኗል ብለዋል በንግግራቸው ።

የአገሪቱን  ቀጣይ ህልውናና የህዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስም አዲሱ አመራርም  ፍቅርን ፣ ይቅርታና መደመርን መሠረት በማድረግ በጎ እርምጃዎችን በመውሰድ አገሪቱ የተጋረጠባትን  አደጋ ለማስወገድ  መቻሉን በንግግራቸው ጠቁመዋል ።

ፕሬዚደንት  ሙላቱ በንግግራቸው የዜጎችን  ሰብዓዊ መብትን ለማስከበርና አገራዊ የፖለቲካዊ  ምህዳሩን  ለማስፋት  በሺዎች  የሚቆጠሩ  ዜጎች ከአሥር በይቅርታ እንዲፈቱ  መደረጉንና ይህም  ለአብነት  የሚነሳ  ለውጥ መሆኑን አመልክተዋል ።

መንግሥት በውጭ አገር ከሚገኙ የፖለቲካ  ድርጅቶች ጋር ድርድር በማድረግ በአገራቸው  የፖለቲካ  ምህዳር ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መደረጉ ሌላኛው  የለውጡ ፍሬ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም በማውረድ ፣ አገራቱ የሰላም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ በመደረጉና በአፍሪካ  ቀንድ ዘላቂ መረጋጋት  ተጨባጭ ውጤት ላስመዘገቡት አስተዋጽኦ ላደረጉት  የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድና ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምስጋና አቅርበዋል ፕሬዚደንቱ ።

በአገሪቱ የፍትህና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከርም የተቋማትንና አሠራሮችን  በማየት  ማሻሻያዎችን ለማድረግ  እየተሠራ  መሆኑንም ፕሬዚደንቱ  በንግግራቸው ጠቁመዋል ።

የሚዲያና የሓሳብን  በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማስከበርም እንዲሁም ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ተሳትፎን ለማሳደግም  የምርጫና  የተለያዩ  የስብዓዊ መብት ህጎችን   ለማሻሻል  እንቅስቃሴዎች መጀመራቸወን  ፕሬዚደንቱ  በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግረዋል ።

በአገሪቱ ትኩረት ተሠጥቶት ተግባራዊ  እየተደረገ ያለው  የዕድገትና  ትራንስፎርሜሸን ዕቅድም  በድርቅ ፣ በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሸቀጦች ዋጋ መቀነስ ምክንያት አፈጻጸሙ የመቀነስ ሁነታ  ማሳየቱንም ፕሬዚዳንቱ  በንግግራቸው አመልክተዋል ።

ፕሬዚዳንት ዶክተር  ሙላቱ  ተሾመ  መንግሥት በ2011 ዓም በኢኮኖሚ ዘርፍ  የሚወስዳቸው  እርምጃዎች   እንደሚከተለው  ዘርዝረዋል   

  • የተረጋጋ  የማይክሮ ኢኮኖሚን ለማጠናከር  አበክሮ ይሠራል
  • ስትራቴጂክ  የኢኮኖሚ  ማጠናከሪያ ሥራዎችን ለማካሄድ  በፈጠራ የታገዙ  ሥራዎች ይሠራሉ
  • የመንግሥት ወጪን  በቁጠባ  የማውጣትና የመጠቀመ ዝንባሌ እንዲኖር ይደረጋል
  • የመንግሥት ገቢ ግብር አስባሰብን  በዘመናዊ መንገድ የመሰብሰብ ሂሰተ ይኖራል ።
  • የፐብሊክ ኢንቨስትመንት  ሥራ  ላይ ልዩ  ትኩረት  ይሠጣል ።
  • የነጻ ገበያ ሥርዓትንና ውድድርን መሠረት ያደረገ ንግድ እንዲኖር ይሠራል
  • አስተማማኝ የውጭ  ንግድን  የማመቻቸት  ሥራዎች  ይከናወናሉ
  • በአጭር ጊዜ  የቀጠናዊ  ኢኮኖሚ ውህደትን ለመፍጠር ይሠራል
  • የአገሪቱን  የቱሪዝም ፍሰትን ለማጠናከር  በርካታ ዕቅዶእ ተግባራዊ ይደረጋሉ
  • የአገሪቱ  የዓለም አቀፍ  የንግድ ድርጅት አባል እንድትሆንበትኩረት ይሠራል
  • በግብርና  ምርታማነት  እንዲጨምረ በትኩረት ይሠራለ ።
  • የሥራ ዕድል  ፈጠራውን  የተሳካለ ለማድረግና የግል ባላሃብቱ መሪ ሚና እንዲጫወት የፖሊሲና የህግ ማሻሻያዎች ያካሄዳሉ
  • የአገሪቱ  የንግድ ህግም  በዚህ ዓመት እንዲጠናቀቅ ይደረጋል ።
  • የአገሪቱን የወጪ ንግድ  ለማሳደግም የሚያስችሉ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለዋል  ።