የእንግሊዝ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የፈጠራ ስራዎች ገበያውን እንዲቀላቀሉ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ እንደሚፈልጉ ገለጹ

የእንግሊዝ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የፈጠራ ስራዎች ወደ ምርት ተቀይረው ገበያውን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በሚሰራው ስራ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍስ እንደሚፍልጉ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉር የንግድ ሚኒስቴር ኢማን ዋዲ ስምዝ የተመራ 21 የሚደርሱ ትላልቅ ኩባንያ አመራሮች የተሳተፉበት invest Africa የልዑካን ቡድን ከኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር በኢትዮጵያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ልዑካኑም ኢትዮጵያ በመንግስት ይዞታ ስር የነበሩ ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር መወሰኗን ተከትሎ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ግልፀዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለልዑካኑ አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም ልዑካኑ አድንቀዋል፡፡

ከቡድኑ ጋር የቀድሞው የእንግሊዝ የአፍሪካ ሚኒስትር ማርክ ሲሞንድስና የኢንቨስት አፍሪካ ስራ አስፈፃሚ ካረን ቴለር ይገኙበታል፡፡ (ምንጭ፡-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት)