ቻይና በ2035 የአየር ማረፊያዎቿን ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ እየሰራች ነዉ

ቻይና ከሁለት አስርተ ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የአየር ማረፊያዎቿን ቁጥር በእጥፍ ለመጨመር እንደምትሰራ አስታውቃለች፡፡

አየር ማረፊያዎቹ አገልግሎት መሥጠት ሲጀምሩም በዓመቱ  ቢያንስ ከ1ነጥብ5 ቢሊየን ተጓዦችን ማስተናገድ እንደሚቻል ነው የሃገሪቷ ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር የገለጸው፡፡

ቻይና አሁን ያሏት አየር ማረፊያዎች  ቁጥር 234 ሲሆን በሚቀጥሉት 17 አመታት ውስጥ 450 ለማድረስ ነው የሃገሪቷ የሲቪል አቬሽን አስተዳደር ያስታወቀው፡፡ 

ቻይና በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ተፅእኖ ፈጣሪ እንድትሆን ለማስቻል ሀገሪቷ ያላትን የአውሮፕላን ማረፊያዎች ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ እየተሰራች እንደሆነ ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው፡፡

ይህ እቅድ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር እስከ 2035 ባለው ጊዜ ውስጥ አውን እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡ (ሲጂቲኤን)