ሰላም ጠቅሞናል፤ ሁከት ደግሞ ይጎዳናል!

በፌዴራላዊ ሥርዓታችን እውን የሆነው ሰላማችን በሁሉም መስኮች ተጠቃሚ እያደረገን ነው። በአንፃሩም በማንኛውም አካባቢ የሚፈጠሩ ሁከቶች ደግሞ እንደሚጎዱን ግልፅ ነው። ባለፉት 26 ዓመታት ከሰላም ያተረፍናቸው ጉዳዩች በርካታ ናቸው። በዚህም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየደረጃው ተጠቃሚ መሆን ችሏል።

በአንፃሩም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረው ሁከት የሰላምን ውድነት እንድንገነዘብ ያደረገን ነው። የሰላም ዋጋ ምን ያህል ከፍተኛ መሆኑንም ያየንበት ነው። በወቅቱ የንፁሃን ዜጎች ህይወት ማለፍ፣ የአካል መጉደልና የንብረት መውደም ለሰላም ያለንን አተያይ እንድንቀይር ያስቻለን ክስተት ነው ማለት እችላለሁ።

በአገራችን ዕውን እየሆነ ያለው ስርዓት ሰላምን ማረጋገጥ በመቻሉ፤ በማህበራዊ መስተጋብሮች ምክንያት የሚፈጠር ልዩነቶችን ለማቻቻል አብሮ ለመጓዝና የማንነት ልዩነቶችን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ለማስተንፈስ አግባብነት ያለው የፖለቲካ መሳሪያ ሆኗል። ይህ አብሮነትም ዜጎች የጋራ ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ ፌዴራሊዝም የጎላ ሚና እንደሚጫወት እምነትን አስይዞ በአዲስ የአስተሳሰብ መንፈስ ወደ ልማት ጎዳና መትመም እንዲችሉ አድርጓቸዋል።  

እናም ስርዓቱ እነዚህን ሁሉ ውጣ ውረዶችን አልፎ ሰላምን ዕውን ያደረገ፣ ልማትን ያረጋገጠና በዚህም የህዝቦችን ፍትሃዊ የሃብት ተጠቃሚነትን ዕውን ያደረገ እንዲሁም ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታን መገንባት ችሏል። ይህ ሲሆን ግን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም። ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩት ሁከትና ግጭቶች ለዚህ ዓይነተኛ ማሳያ ይመስሉኛል።

ያም ሆኖ ህዝቡ በሰላሙ ላይ ስለማይደራደር ለግጭት ኃይሎች የሚሆን ምቹ ምህዳር እንዳይኖር አድርጓል። ምንም እንኳን በመንግስት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ አንዳንድ ግለሰቦች የተሰጣቸውን ህዝባዊ አደራ መወጣት የማይችሉና የማይፈልጉ፣ ለግል ጥቅማቸው ያደሩ አልፎ አልፎ ደግሞ ድብቅ የጥፋት ኃይሎች ፖለቲካዊ ተልዕኮ ይዘው የሚነቀሳቀሱ ሆነዋል።

በዚህም በመልካም አስተዳደርና በሙስና ህዝቡን ሲያማርሩት እንደነበር የሚታወቅ ነው። እነዚህ ሃይሎች የፈጠሩት ምሬት ከትምክህትና ከጥበት አራማጆች አጀንዳ ጋር ተዳምሮ የሀገራችንን ሰላም ማወኩ የቅርብ ጊዜ ትውሰታችን ነው።

ይህ ሁከት ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አካባቢዎች ብቅ ጥልም እያለ በመታየት ላይ ይገኛል። ግና ከሁከት የሚገኝ ምንም ዓይነት ጥቅም እንደሌለ ማንም የሚያውቀው ነው። የሁከቱ አራማጆችም እንደ ኤርትራ መንግስት ዓይነት የአገራችንን ሰላም ለማወክ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሃይሎች እንጂ ከሀገራችን ሰላም ወዳድ ህዝብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። ህዝቡ ከመልካም አስተዳደርና ከብልሹ አሰራር ጋር ተያይዞ ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎች መንግስት አቅም በፈቀደ መጠን ምላሽ እየሰጠ ነው። ከዚህ በመለስ የሁከቱ ባለቤቶች ሌሎች ናቸው—ፀረ ሰላም ሃይሎችና አጋፋሪዎቻቸው።

በተለይም የኤርትራ መንግስት ሁከት መፍጠርን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል። የኤርትራ መንግስት ከአንዳንድ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ገንዘብ በገፍ እየተቀበለ ጥቂት ፅንፈኞችን በማሰማራት በየማህበራዊ ሚዲያው እንዲሁም ኢሳት በተሰኘው የሁከት ማቀነባበሪያ ጣቢያው አማካኝነት አሉባልታን ከመንዛት አልተቆጠበም። አንዳንድ ወገኖችም ሳያውቁ የዚሁ አሉባልታ ሰለባ መሆናቸው አልቀረም። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለያዩ ፎቶዎችን በማቀናጀት በሩቅ ምስራቅ ሀገራት ውስጥ የተከናወኑ ድርጊቶችን እዚህ ሀገር የተፈጠሩ በማስመሰል አንዳንድ ወገኖችን ሲያደናግሩ ይታያሉ። እዚህ ላይ በምሳሌነት ባንግላዴሽ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ሲጫወት የነበረና ቦንቡ ፈንድቶ የተጎዳ የአንድ ህፃን ልጅን አካል በፌስ ቡክ ላይ በማሳየት ‘ኢትዮጵያ ውስጥ ህፃናት በአውሮፕላን እየተደበደቡ ነው’ የሚል አስገራሚ የፈጠራ ድርሰትን ማንሳት ይቻላል። እናም የሽብር ቡድኑ አባላት ሌሎች ፎቶዎችንም ‘በፎቶ ሾፕ’ ቴክኖሎጂ ጥበብ በማቀናጀት ያልተደረገን ጉዳይ ተከናወነ በማለት አንዳንድ ወገኖችን ለማሳሳት እየሰሩ መሆኑ ሊታወቅ የሚገባ ይመስለኛል።

እርግጥ የሽብር ቡድኑ በተለያዩ ወቅቶች ህዝብን ከማደናገር የተቆጠበት ጊዜ የለም። በተለይም እዚህ ሀገር ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማያውቀውን የዋህ ዲያስፖራ በተለያዩ መንገዶች ያጭበረብሩታል። መሪውን ጨምሮ የቡድኑ አባላት ፍላጎታቸው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በልማታዊ ዕድገቱ ድል ምክንያት የሚፈጠሩ ነባራዊና ጊዜያዊ እንቅፋቶቸን ተመርኩዘው በውጭ የሚገኙ ጥቂት ደጋፊ ዲያስፖራቸውን እያደናገሩ የጥቂት አመራሮቻቸውን ኪስ ማደለብ ነው። ይህን ለማስፈፀምም አይናቸውን በጨው ታጥበው የአሉባልታ እምቢልታቸውን ከመንፋት ወደ ኋላ አይሉም።

እናም ሃሳባቸው በሙሉ የራሳቸው አጀንዳ ሳይኖራቸው በሌሎች አጀንዳዎች ላይ በመንጠላጠል የሽብር ቡድኑን “በገቢ ማሰባሰቢያ ዘዴ” ማጎልበት ነው—ሁከት መፍጠር አንድ የስራ መስክ ነውና። ይሁን እንጂ ይህንን ሃቅ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ ይገነዘበዋል። ሁከት ለኤርትራ መንገሰትና ለእነዚህ የሽብር ሃይሎች እንጂ ለማንም እንደማይጠቅም ይረዳል።

የኤርትራ መንግስት ከአንዳንድ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ገንዘብ በገፍ እየተቀበለ ጥቂት ፅንፈኞችን በማሰማራት በየማህበራዊ ሚዲያው እንዲሁም ኢሳት በተሰኘው የሁከት ማቀነባበሪያ ጣቢያው አማካኝነት አሉባልታን ከመንዛት አልተቆጠበም። አንዳንድ ወገኖችም ሳያውቁ የዚሁ አሉባልታ ሰለባ መሆናቸው አልቀረም። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለያዩ ፎቶዎችን በማቀናጀት በሩቅ ምስራቅ ሀገራት ውስጥ የተከናወኑ ድርጊቶችን እዚህ ሀገር የተፈጠሩ በማስመሰል አንዳንድ ወገኖችን ሲያደናግሩ ይታያሉ። እዚህ ላይ በምሳሌነት ባንግላዴሽ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ሲጫወት የነበረና ቦንቡ ፈንድቶ የተጎዳ የአንድ ህፃን ልጅን አካል በፌስ ቡክ ላይ በማሳየት ‘ኢትዮጵያ ውስጥ ህፃናት በአውሮፕላን እየተደበደቡ ነው’ የሚል አስገራሚ የፈጠራ ድርሰትን ማንሳት ይቻላል። እናም የሽብር ቡድኑ አባላት ሌሎች ፎቶዎችንም ‘በፎቶ ሾፕ’ ቴክኖሎጂ ጥበብ በማቀናጀት ያልተደረገን ጉዳይ ተከናወነ በማለት አንዳንድ ወገኖችን ለማሳሳት እየሰሩ መሆኑ ሊታወቅ የሚገባ ይመስለኛል።

እርግጥ የሽብር ቡድኑ በተለያዩ ወቅቶች ህዝብን ከማደናገር የተቆጠበት ጊዜ የለም። በተለይም እዚህ ሀገር ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማያውቀውን የዋህ ዲያስፖራ በተለያዩ መንገዶች ያጭበረብሩታል። መሪውን ጨምሮ የቡድኑ አባላት ፍላጎታቸው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በልማታዊ ዕድገቱ ድል ምክንያት የሚፈጠሩ ነባራዊና ጊዜያዊ እንቅፋቶቸን ተመርኩዘው በውጭ የሚገኙ ጥቂት ደጋፊ ዲያስፖራቸውን እያደናገሩ የጥቂት አመራሮቻቸውን ኪስ ማደለብ ነው። ይህን ለማስፈፀምም አይናቸውን በጨው ታጥበው የአሉባልታ እምቢልታቸውን ከመንፋት ወደ ኋላ አይሉም። እናም ሃሳባቸው በሙሉ የራሳቸው አጀንዳ ሳይኖራቸው በሌሎች አጀንዳዎች ላይ በመንጠላጠል የሽብር ቡድኑን “በገቢ ማሰባሰቢያ ዘዴ” ማጎልበት ነው—ሁከት መፍጠር አንድ የስራ መስክ ነውና።

እርግጥ ይህ “ዘዴ” እስከ የት ድረስ እንደሚሰራ ለእነርሱ ትርጉም አልባ ይመስለኛል። ብቻ አጀንዳ ከተገኘ እንደ አንድ የገቢ ማግኛ መንገድ ጉዳዩን በማጦዝ “አካኪ ዘራፍ” ይላሉ።

ከሁከት ፈጣሪዎቹ ውስጥ ራሳቸውን ግንቦት ሰባትና ኦነግ እያሉ የሚጠሩት የሽብር ሃይሎችን መመልከት እንችላለን። እነዚህ ሁከት ፈጣሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የሚያነጋግር ነባራዊ ጉዳይ ካገኙ፤ ባህር ማዶ ቁጭ ብለው አይስክሬም እየላሱ ተራ ቃላት ጨዋታን በመምረጥ እዚህ ሀገር ውስጥ ሁከት ለመፍጠር የሚሯሯጡት አሸባሪዎቹና ጀሌዎቻቸው ሎተሪ የደረሳቸው ያህል ይጨፍራሉ። እናም አጀንዳውን የግል ጉዳያቸው በማድረግ በኢሳትና በፌስ ቡክ ላይ እንደ አቡነ ዘ- ሰማያት ሲደጋግሙት ይከርማሉ።

ግባቸው አጋጣሚውን በመጠቀም ሊገኝ ከሚችል ሁሉንም የማግኘት የዜሮ ድምር ፖለቲካን ማራገብ እንጂ፤ ከህዝብ ተጠቃሚነት ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ የሰው ልጅ ሰቆቃ ለእነርሱ ምናቸውም አይደለም።

የሽብር ቡድኖቹና አባላቶቻቸው በተለያዩ ወቅቶች ከሚጠቀሙባቸው የሁከት ማቀጣጠያ ጉዳዩች ውስጥ አንዱ የሃይማኖት ጉዳይ ነው። በተለይም በሙስሊሞች ጉዳይ ጣልቃ በመግባት በአጀንዳ ቅብብሎሽ በሽብር ቡድኑና በልሳኑ ኢሳት የስበት ማዕከል አማካኝነት  ለመፍጠር የሞከሩት “የአየር ላይ አመፅ” ጠብ  የሚል ፍሬ ባያስገኝላቸውም ጉዳዩን በማጎን ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ይታወሳል።

ከዚህ በተጨማሪ በክርስትና ሃይማኖት ውስጥም ስደተኛውን ሲኖዶስ በመደገፍ ቤተ-ክርስቲያኗን በሪሞት ኮንትሮል ለመምራት ሞክረዋል። እርግጥ ሁሉም ጥረታቸው መና ቀርቷል። ለዚህ ደግሞ ሁለት ምክንያቶችን በዋነኛነት መጥቀስ የሚቻል ይመስለኛል። የመጀመሪያውና ግንባር ቀደሙ ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ ማህበረሰብ ሰላም ወዳድ ከመሆኑም በላይ፣ መንግስት በጉዳዩ ላይ የሚከተለውን አካሄድ ሙሉ በሙሉ በመገንዘቡ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ መንግስት በሃይማኖትና በአሰራሩ መካከል ያለውን ድንበር በማይጥስ መልኩ የሁሉንም ምዕመናን ጥያቄዎችን በህገ መንግስቱ አግባብ በማያሻማ ሁኔታ መመለስ በመቻሉ ነው።

ያም ሆነ ይህ ግን እነ ግንቦት ሰባትና ጀሌዎቻቸው በሁከት አምላኪነት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም። በእነዚህ የሽብር ቡድኖች ትስስርም እንደ ፌስ ቡክ ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች በአሉባልታ ሁከትን ይጋግራሉ። የጋገሩትም እንጀራ ሆኖ ገቢ እስከሚያስገኝላቸው ድረስ ያለመታከት ይሰራሉ። እዚህ ሀገር ውስጥ የሚፈጠር ነገር ለእነርሱ የገቢ ማስገኛ በመሆኑ፤ አንዱን ብሔር ከሌላው በማባለት የሁከት ሴራን ይጠነስሳሉ።

ታዲያ ይህን ሁኔታ የአገራችን ህዘቦች በጥልቀት ሊገነዘቡት ይገባል። ሁከት ለፈጣሪዎቹ መጠቀሜያ የመሆኑን ያህል ለአገራችን ህዝቦች ደግሞ ሞትን፣ አካል መጉደልን፣ ንብረት ማውደምንና መሰደድን ያስከትላል። እናም ሁከት ባለፉት 26 ዓመታት በሰላማችን ውስጥ ያገኘናቸውን ሁለንተናዊ እድገቶች በመጎተት ወደ ኋላ የሚመልሰን ስለሆነ ሁሉም ዜጋ ሊኮንነው ይገባል።