የእንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መውጣትን ተከትሎ ተቋማት ወደ ፈረንሳይና ኔዘርላንድ ከተሞች ሊዘዋሩ ነው

የእንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መውጣትን ተከትሎ ቁልፍ የቢዝነስ ተቋማት ከለንደን ወደ  ፈረንሳይና ኔዘርላንድስ ከተሞች ሊዛወሩ መሆኑ ተገለጸ ።    

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት በመውጣት ከህብረቱ ጋር የነበራትን የነፃ የንግድ ስምምነት ለማስቀጠል 40 ቢሊዮን ፓውንድ እንዲትከፍል ተጠየቀች፡፡

እንግሊዝ የፋይናንስ እና የመድሓሃኒት ነክ ምርቶች የገቢያ ማዕከል እንዲትባል ካስቻሉት ነገሮች አንዱ ሀገሪቱ የአውሮፓ ህብረት የንግድ እና ኢንቨስትመንት መዲና ሆና መቆየቷ ነው፡፡  

በእንግሊዝ  ታላቅ የተባለለትን የሥራ ዕድል ፈጥረው የነበሩ እነዚህ ተቋማት ወደ ፓሪስ እና አምስተርዳም የሚያመሩ መሆናቸው ደግሞ በእንግሊዝ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ዜጎች ሥራ እንዲፈቱ የሚያደርጋቸው ነው ተብሏል፡፡  

ቁልፍ የአውሮፓ ህብረት ተቋማትን በማቀፍ አቻም ያልነበራት የእንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷ ለፈረንሳይ እና ኔዘርላንድ መልካም ዜና ነው የሚባለውም በዚህው ምክንያት ነው ፡፡

የአውሮፓ ህብረት ውሳኔውን በብራሴልስ እንዳሳለፈው የህብረቱ የመዳሓኒት ነክ ተቋማት መቀመጫውን ወደ አምስተርዳም እንዲያዛውረው እና የአዉሮፓዉያን የባንክ እና ፋይናንስ ማዕከል ደግሞ ወደ ፓሪስ ይዛወራል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

ሁለቱ ታላላቅ የአውሮፓ ህብረት አባላት ፈረንሳይ እና ነዘርላንድ ህብረቱ ሁለቱን ታላላቅ ተቋማት ወደ ሀገራቸው ለመውሰድ ከፍተኛ ግፊትም ሲያረጉ ከርሟል፡፡ ተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ፣ የኢንደስትሪ እምብርት የመሆን አቅም ያላቸዉ እና የሀገራቱን ክብር ለማስቀጠል ታላቅ ሚና ያላቸው እንደመሆናቸው ጥቅማቸው የዋዛ እንዳልሆነ ተወስቷል፡፡

እንግሊዝ ከህብረቱ ሲትወጣ የሀገሪቱ ባንኮች የፓስፖርት መብታቸውንም ጭምር ያጣሉ፡፡ በተለይ የመድሓኒት እና የፋይናንስ ተቋማቱ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ በሚፈጥሩት የስራ ዕድል ለሀገራት ምጣነ ሀብት የሚያበረክቱት ሚና የላቅ  ነዉ፡፡  የቢሪኤግዚት ዋና ፀሃፊ የሆኑት ዴቪድ ዴቪስ ብሪተን ከአውሮፓ ህብረት ብትወጣም እነዚህን ተቋምት ግን ይዛ ትቆያለች በሚል ዜጎቻቸዉን አሳስቷል በሚል ተተችቷል፡፡

እናም የአዉሮፓ ህብረት ካውንሲል ፕሬዝዳንት ዶናልድ  ከ27 የህብረቱ አባል ሀገራት የ19 ሀገራት ከተሞች ሲፎካከሩ ቆይተው ውስብስብ የሆነውን መስፈርት በማሟላት ግን ፓሪስ እና አምስተርዳም ተመርጧል ብለዋል፡፡

የቢሪኤግዚት ፀሃፊው ደቪድ ዴቪስ ግን ሀገራቸው ከህብረቱ ጋር ስምምነት ላይ ላለመድረሳቸው ፈረንሳይ እና ጀርመንን  ወቅሷል፡፡ ሀገራቱ በህብረቱ እጃቸው ረጅም በማለት የብሪተን ጥቅም መንካታቸውንም አንስቷል፡፡

እንግሊዝ ከአዉሮፓ ህብረት የመዉጣት ዉሳነ ላይ ካደረሳት አንዱ ምክንያት በህብረቱ የሚሰጣት የስደተኞች ቁጥር መበራከት ነው፡፡

የእንግሊዝ  ከህብረቱ መውጣትን ተከትለው የጀርመን የብዝነስ ተቋማት ግን ሐገሪቱ በህብረቱ አንዲትቆይ ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸዉ፡፡

የጀርመን ኢንደስትሪ ፌደሬሽን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሄነሪክ ዌይስ የአውሮፓ ህብረት የውድድር መንፈስ የሚትፈጥረውን በጣም ጠቃሚ አጋሩን አቷል ብሏል፡፡ ፌዴሬሽኑ ግን ለውድድሩ ሲባል ዩናይትድ ክንግደም በንግዱ ግንኙነት ከህብረቱ ጋር እንዲትቆይ ነዉ ፊላጎታቸዉን ያሳዩት፡፡

 የእንግሊዝ መንግስትም ቢሆን ከህብረቱ የመውጣቱን ውሳኔ እንደገና ማጠን እንዳለበት አሳስቧል፡፡ የኢንደስትሪ ማህበሩ ረጂም እጅ ያለው በመሆኑ በብሪ ኤግዚት ላይ እየተደረገ ባለው ድርድር ውሳኔዎችን በማስቀየር ሚና ሊኖራቸዉ ይችላል ተብሏል፡፡

እንግሊዝ መስፈርቶችን የሚታሟላ ከሆነ ግን ምናልባትም ለሀገሪቱ የአዉሮፓ የነፃ ንግድ ስምምነት ውስጥ ተሳታፊ ሊትሆን እንደሚትችል ተጠቁሟል፡፡ ለዚህ ደግሞ እንግሊዝ 40 ቢሊየን ፓዉንድ በቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ ይጠበቅባታል፡፡