6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እየተካሄደ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እየተካሄደ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከአሁን ባሰባሰበው መረጃ መራጩ ህዝብ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

በቀጣይም ተመሳሳይ መረጃዎችን ከፌዴራልና ከክልል እንዲሁም ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እያሰባሰበ ተአማኒነት ያለው፣ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ እንደሚያደርግ ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል፡፡