646 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ነሀሴ 17/2013 (ዋልታ) – በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት በዛሬው ዕለት 210 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 646 ኢትዮጵያዊያን ከጂዳ፣ ሳዑዲ አረቢያ ተመልሰዋል፡፡

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡