82ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል እየተከበረ ነው

ሚያዚያ 27/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያውያን አርበኞች የጣልያንን ወራሪ ኃይል ድል ያደረጉበት 82ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል አራት ኪሎ በሚገኘው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ኃውልት በመከበር ላይ ይገኛል።

“አብሮነት ለጽናትና ድል” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የመታሰቢያ በዓል ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከድል ሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በበዓሉ ላይ አባት አርበኞች፣ እናት አርበኞች፣የአርበኛ ቤተሰቦች፣የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣የአገር መከላከያ ሰራዊት ተወካዮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።