89 ሺሕ ዶላር የሚያወጡ 17 ቬንትሌተሮች ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ተደረጉ

ታኅሣሥ 6/2014 (ዋልታ) የቦስተን ታክስ ፎርስ ከቦስተን የኢትዮጵያውያን ስፖርት ክለብ ጋር በመተባበር 89 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ 17 ቬንትሌተሮች ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ፡፡

ክለቡ በኢትዮጵያ ለአሜሪካ ኢምባሲ ያስረከቧቸው ቬንትሌተሮች ለጤና ሚኒስቴር መላካቸውን ነው አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስታወቁት፡፡

አምባሳደር ፍጹም ክለቡን እና ማሽኖቹን በመመርመር ጭምር ሙያዊ ድጋፍ የሰጡትን አቶ እሸቴ ወልደየስን እና ቬንትሌተሮቹ እስኪጫኑ የመጋዘንና ተያያዥ ወጪዎችን ለሸፈነው ለናታን ትራቬል እና ካርጎ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በማመስገን ሌሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ እምነታችን ነው ብለዋል፡፡