9ኛው የሕንድ-አፍሪካ አይሲቲ ኤክስፖ ተከፈተ


ነሐሴ 3/2015 (አዲስ ዋልታ) ዘጠነኛው የሕንድ-አፍሪካ አይሲቲ ኤክስፖ ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት መሰንበት ሸንቁጤ በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት ሼቲኪንቶንግ ጨምሮ የዘርፉ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ታድመዋል።

ኤክስፖውን የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከሕንዱ ቴሌኮም ኢኩዩፕመንት እና አገልግሎት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ነው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ 30 የሕንድ አይሲቲ እና 16 የኢትዮጵያ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል።

ኤክስፖ የአይሲቲ የስራ ፈጣሪዎችን ግዙፍ ኩባንያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ባለቤቶችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ መሆኑ ተመላክቷል።

እንዲሁም የኢትዮጵያን የ2025 የዲጂታል ስትራቴጂ ለባለድርሻ አካላት በማስተዋወቅ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለውም ኢዜአ ዘግቧል፡፡