ለሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

   
ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ግዳጅ ቀጠና ያመራው የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ዋና አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር መሃመድ አህመድ የተመራው የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት አዲስ አበባ ሲደርሱ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታና በሌሎች አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ሃገራዊ ጥሪውን ተቀብሎ በመምጣቱ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ክልሉ ከሌሎች ሀገራት ጋር በሚዋሰንበት አካባቢ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሽብርተኝነት የተፈረጁትን እንደ አልቃይዳ እና አልሸባብ የመሰሉ አሽባሪ ድርቶችን በመደምሰስ አኩሪ ድል እንደፈፀመ ይታወቃል።