ለቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው የምስጋና ዝግጅት ተካሄደ

ሰኔ 02/2013(ዋልታ) ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለትምህርት ዘርፍ ለበረከቱት አስተዋጽኦ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት የምስጋና ዝግጅት ተካሄደ።

በቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው አማካኝነት በመጀመሪያው ዙር 20 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ በሁሉም ክልሎች አስገንብተዋ ተብሏል።

በሁለተኛው ዙር ስምት ትምህርት ቤቶች በ128 ሚሊዮን ብር ግንባታቸውን የማስጀመር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ቀዳሚዊ እመቤቷ ትምህርትን ለማስፋፋት በቁርጠኝነት እየሰሩ ነው የተባለ ሲሆን ብዙ ሺህ ተማሪዎች የነገ ቀናቸውን ያማረ ለማድረግ በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ  ማድረጋቸው ነው የተነገረው።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ መገንባት  ብዙ ርቀት ተጉዘው የሚማሩ ተማሪዎቹ  ሆነ በዳስና በዛፍ ጥላ  ውስጥ ትምህርት የሚማሩትን ደረጃውን በጠበቀ ትምህርት ቤት እንዲማሩ ማድረግ  እንደተቻለም ነው የተገለጸው።

ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ድጋፍ ለሚሸ አካል ጉዳተኞችን በመደገፍም አስተዋጽኦቸው ከፍተኛ ትልቅ ነው የተባለ ሲሆን በአዲስአበባ  ከተማ 300 አይነስውራንን ማስተማር የሚችል ትምህርት ቤት በ400 ሚሊዮን ብር እያስገነቡ መሆኑ ተነግሯል። ልዩ ፍላጎት ማስተማሪያ እየተገነባ ባለው የዲቦራ ፋውንዴሽን ውስጥ እያስገነቡ መሆኑ ተገልጿል ።

ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው በትምህርት ዘርፋ እያበረከቱት ባለው አስተዋጽኦ ባለቤታቸው ጠቅላይ ምኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሁለት መጽሐፎቻቸው ሽያጭ ያገኙትን ገቢ ለትምህርት እንዲውል አድርገዋል።

(በምንይሉ ደስይበለው)