ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቻግኒ ከተማና ጓንጓ ወረዳ ህዝብ ጋር እየተዋያዩ ነው

ሰኔ 2/2013 (ዋልታ) – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቻግኒ ከተማና ጓንጓ ወረዳ ህዝብ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

በውይይቱ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፣ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የከተማውና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከህዝቡ የተወጣጡ ተወካዮች ተገኝተዋል።

መድረኩ በምርጫና ወቅታዊ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።