በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ሴቶች ይበልጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና የአመራር ሰጭነት ሚናቸው እንዲያድግ ሁሉም የዴሞክራሲ ተቋማት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሴቶችን ተሳትፎና ውክልና ለማሳደግ ከፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ወይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ በሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የኮከስ አባላት፣ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
የሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ፣ በማኅበረሰብ ደረጃ ያለውን ለሴቶች የሚሰጠውን አመለካከት በመቀየር ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጭነት እንዲበቁ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ የሴቶች ተሳትፎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕግ አውጭው የመንግሥት መዋቅር 37 ነጥብ 8 በመቶ መድረሱን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ በክልል ሕግ አውጭ ደረጃም ውክልናቸው 40 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል።
ሴቶች የአመራር ሰጭነት እና የፖለቲካ ተሳትፏቸው እንዲጎለብት የፖለቲካ ፖርቲዎች አሳታፊ የሆነ ሥርዓት መዘርጋት እናዳለባቸውም ተጠቁሟል።
በመድረኩ “በሴቶች የአመራር ውሳኔ ሰጭነት ዙሪያ የተካሄደ አገራዊ የጥናት ግኝት የቀረበ ሲሆን፣ ሴቶች በከፍተኛ፣ በመካከለኛ እንዲሁም በዝቅተኛ የአመራር እርከን ያላቸውን የውክልና ቁጥር መጨመር እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
(በሳራ ስዩም)