ኮርፖሬሽኑ ለተለያዩ አገልግሎቶች እያስገነባ ያለውን ቤቶች እያጠናቀቀ ነው

ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሚያስገነባቸውን ለንግድ ለመኖሪያ እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሳይቶች ግንባታ እያጠናቀ መሆኑን አስታወቋል።

በግንባታ ላይ ከሚገኙት 10 ሳይቶች መካከል 9ኙ በተለመደው የግንባታ ሒደት እንዲሁም 1ሳይት ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቅርቡ ለተገልጋዮች እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡

በግንባታ ወቅት ከውጭ የሚገቡ እቃዎች አቅርቦት እጥረት እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ መከሰት ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እክል እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ይህን ችግር በመፍታት ግንባታውን ለማጠናቀቅ በስራ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
(በዙፋን አምባቸው)