በህግ ማስከበር ሂደቱ ጉዳት ያጋጠማቸው ወገኖች ያሉባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

በአላማጣ፣ መኾኒ፣ ጨረጨር፣ ዳንሻ፣ ማይካድራ እና ሌሎች በህግ ማስከበር ሂደቱ ጉዳት ያጋጠማቸው ወገኖች ያሉባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋማት ከሰላም ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋሙ ብሔራዊ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ጋር በትብብር በርካታ የምግብና ቁሳቁስ ጭነት በዛሬው ዕለት ሽሬ ከተማ ማድረሳቸው ተገልጿል።

ስርጭቱ እንደየ ጉዳት መጠን ቅድሚያ እየተሰጠ በተደራጀ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ድጋፉ ማህበረሰቡን መልሶ እስከማቋቋም የሚዘልቅ ሲሆን የተደራሽነት ክትትል በሚመለከታቸው አካላት በአትኩሮት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።