ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – በላሙ ወደብና ተዛማጅ ፕሮጀከቶች አሁናዊ ሁኔታና በቀጣይ አፈጻጻጸም ዙሪያ ምክክር እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን የትራንስፖርትና ሌሎች የሚመለከታቸው ሚኒስትሮች በተገኙበት የላሙ ኢትዮ ደቡብ ሱዳን ወደብን የተመለከተ ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በምክክሩ የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ህብረት የመሠረተ ልማት ልዩ ልዑክ ራይላ ኦዲንጋ ተሳትፈዋል።
በመድረኩም በላሙ ወደብና ተዛማጅ ፕሮጅከቶች አሁናዊ ሁኔታና ቀጣይ አፈጻጻጸም ዙሪያ ተሳታፊዎቹ መመካከራቸው ተገልጿል።
የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የመሠረተልማት ግንባታ በአገሮች መሀከል ዘላቂነት ያለው ልማት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
እስከ ሰኔ 24 2013 ዓ.ም በሚቆየው ምክክር የኬንያ እና ደቡብሱዳን የልዑካን ቡድን የመስክ ጉብኝት በኢትዮጵያ እንደሚደርጉ ኢዜአ ዘግቧል።