በምእራብ ወለጋ የተገነባው ኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

ሰኔ 06/2013 (ዋልታ) – በምእራብ ወለጋ በማና ስቡ ወረዳ መንዲ ከተማ አቅራብያ የተገነባው ኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተመረቀ፡፡
በምርቃት ስረዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ውሀ መስኖና ኢኔርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፕሬዝዳንት አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይህ ትምህር ቤት ግንባታው በተያዘው የበጀት ዓመት ከስድስት ወር በፊት የተጀመረ ሲሆን 18 ብሎኮች አሉት ነው፡፡
በቂ የመማሪያ ክፍሎቸ፣ ቤተ-መጽሃፍት፣ ቤተ-ሙከራ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው።
የክልሉን ህዝብ የልማት ፍላጎት ለሟማላት የክልሉ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ በተለይም በምዕራብ ወለጋ ላይ አራት ዋና ዋና ኢኒሸቲቮችን በማዘጋጀት እየሰተራ ይገኛል ብለዋል።
ከነዚህ ኢኒሸቲቮች ውስጥ የትምህርት ዘርፍ አንዱ መሆኑን ሽመልስ አብዲሳ አንስተዋል። የተማረ እና በስነ-ምግባር የታነፀን ትውልድ ለማፍራት በመሰረተ ልማት የተሟላ የትምህርት መሠረተ ልማቶች አስፈላጊ መሆኑን ነው የገለጹት።
በዚህም በክልሉ 100 ኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አስገንብቶ እያስመረቀ እንደሚገኝ አስታውሰዋል።
ከነዚህም ውስጥ በምእራብ ወለጋ ዞን በማና ሲቡ ወረዳ መንዲ ከተማ የተገነባው ኢፋ ቦሩ (የነገ ብርሀን) ትምህርት ቤት ዛሬ ተመርቋል።
በክልሉ የሚሰሩ የልማት ስራዎች በዘላቂነት ለማረጋገጥ የህዝብ አንድነት እና የጋራ ሰላም ማስጠበቅ አስፈላጊ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለዚህ ደግሞ ብዙ ችግሮችን ማሸነፍ ተችሎ ዛሬ በዞኖቹ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁ ፕሮጀክቶች ማሳያ ይሆናሉ ብለዋል። ስለዚህም ይህን አንድነቱ ህዝቡ ሰላም እና አንድነቱን እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።
በተያያዘ ዜና በዞኑ ለነጆ ከተማ እና አከባቢው የመብራት ችግር ይፈታል የተበለው ባለ 50 ሜጋ ሀወር ትራንስፎርመር ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመሯል።
(በሚልኪያስ አዱኛ)