በሲዳማ ክልል የዕውቅና መስጠት መርኃግብር

መስከረም 18/2014 (ዋልታ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መዋቅሮች፣ መስሪያ ቤቶች እና ግንባር ቀደም ፈፃሚዎች ዕውቅና የመስጠት ስነሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

13 የመመዘኛ መስፈርቶችን በማለፍ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና እየተሰጠ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

በመርኃግብሩ በአፈፃፀማቸው ግንባር ቀደም የሆኑ ከየተቋማቱ 3 የላቀ ፈጻሚዎች በአጠቃላይ ሁለት መቶ አራት ሠራተኞች እና ዘጠኝ አመራሮች ዕውቅና እንደሚሰጣቸውም ተጠቁሟል፡፡

ክልል አቀፍ የዕውቅና መስጠት መርኃግብር ላይ የሲዳማ ክልል ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳስር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡

በሰለሞን በየነ