መጋቢት 15/2013 (ዋልታ) – የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኙ ከጀመረበት ከባለፈው አመት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ 2 ሚሊየን 746 ሽህ 878 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገለጸ።
በወረርሽኙ ህይወታቸውን ካጡት መካከል 110 ሺህ 744 የሚሆኑት አፍሪካውያን መሆናቸው ተገልጿል፡፡
እስካሁን ድረስ በአለም ላይ 124 ሚሊየን 833 ሺህ 718 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን፣ 100 ሚሊየን 864 ሺህ 255 የሚሆኑ ደግሞ ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ማገገማቸው ተጠቁሟል።
በአለም ዙሪያ በተለያዩ ሀገራት የተሰሩ ክትባቶች እየተሰራጩ ቢሆንም፣ የበሽታው አሳሳቢነት ግን አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ሲጂቲኤንን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል።