በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጥፋተኛ የተባለው ጥላሁን ያሚ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ

ሐምሌ 27/2013 (ዋልታ) – በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጥፋተኛ የተባለው ጥላሁን ያሚ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ።
2ኛው ተከሳሽ ከበደ ገመቹ 18 አመት ሲበየንበት፣ 3ኛው ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ ደግሞ በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ ችሎት ማስታወቁን ኢቢኮ ዘግቧል።