በኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ

መጋቢት 22/2013 (ዋልታ) – በግብርና እና በጤና ሚኒስቴር እንዲሁም በተባባሪ አካላት በጋራ የተዘጋጀ እና በኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ላይ ያተኮረ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

ምክክሩ በኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት አሁናዊ እና መፃኢ እድሎች ያተኮረ እንደሆነ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

በምክክሩ የኢትዮጵያን የምግብ ሥርዓት በመለወጥ በመላ ሀገሪቱ ዘላቂ እና ጤናማ አመጋገብን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ተጨባጭ መፍትሔዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በቀጣይ 2 ወራት ከሚካሄዱ 3 ተከታታይ ምክክሮች የመጀመሪያው የሆነው የዛሬው መድረክ ኢትዮጵያን ለመጪው ዓለም አቀፍ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ከማዘጋጀት ባለፈ በዘርፉ ተጨማሪ ድጋፍ እንድታገኝ ያስችላታልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡