በኦንላይን ለተጎዱ ወገኖች እስካሁን ከ1.1 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በ’eyezonethiopia.com’ መተግበሪያ አማካኝነት በአገር ቤት በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበው ገንዘብ ከ1.1 ሚሊየን ዶላር በላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ከሁለት ሳምንት በፊት ባስተዋወቀውና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የክፍያ መስመሩን ባመቻቸው መተግበሪያ ከ6 ሺሕ 269 ዳያስፖራዎች ከ1.1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።

ኤጀንሲው በድጋፉ ላይ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋናውን አቅርቧል።

ኤጀንሲው ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረቡን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።