በውሃ ዲፕሎማሲ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የመስራት ስልቶችን መከተል እንደሚገባ ተገለጸ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

ነሐሴ 5/2015 (አዲስ ዋልታ) በውሃ ዲፕሎማሲ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የመስራት ስልቶችን መከተል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሉት “ጠንካራ ዲፕሎማሲና ተግባቦት ለዘላቂ የውሃ ሀብት ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ መካሄድ በጀመረው በ9ኛው የውሃ፣ የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙዩኒኬሽን ፎረም ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡

በውሃ ዲፕሎማሲ ላይ ባለን የተግባቦት አቅም መስራት ወሳኝነት እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ በውሃ ላይ የምናከናውናቸውን ስራዎቸ በሳይንሳዊ መንገድና ቋንቋ መናገር፣ የዘርፉ ባለሙያዎችን ማሰባሰብ እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ የመስራት ስልቶችን መከተል እንደሚገባ አንስተዋል።

በመሆኑም መሰል ተግባራትን በምርምር የታገዙ በማድረግና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር መስራት አዋጭ ተግባር ነውም ብለዋል።

በፎረሙ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ሎሎች በውሃ ዲፕሎማሲ የሚሰሩ ግለሰቦቸ ታድመዋል።

በሰሎሞን በየነ