ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78.3 በመቶ ደረሰ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራትንና የህዳሴ ግድቡን የግንባታ ሂደት በተመለከተ መግለጫ እየሰጡት ያሉት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደገለጹት፤ የግድቡ ግንባታ የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል።

አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም ደግሞ 78 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል።

በቀጣይ ወራት የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማሳካት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ግድቡ ለተፋሰሱ አገሮች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ፤ “የግድቡ ግንባታ ሰኔ ወር ላይ ከነበረበት አፈጻጸም የ4 ነጥብ 05 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል” ብለዋል።
(ምንጭ፡- ኢዜአ)