አቶ በላይነህ ክንዴ ከ5 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ለአንድ ወር መመገብ የሚችል የምግብ እርዳታ ለገሱ

 

አቶ በላይነህ ክንዴ በቤንሰንጉል ጉምዝ ክልል ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ-ራንች ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ800 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸውን በቻግኒ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በከታማዋ በጊዜያዊነት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ጀምበሩ ደሴ እንደገለፁት ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ ያደረጉት ድጋፍ ለተፈናቃዮች ጊዚያዊ እፎይታ የሚሰጥ እና ለወገን ደራሽነታቸውን ያሳዩበት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በቻግኒ ከተማ ራንች በተባለው ጊዜያዊ መጠለያ ከ40 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች አንደሚገኙ የአብመድ ዘግቧል።