ግንቦት 23/2013 (ዋልታ) – አንዳንድ ሃገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እያደረጉ ያለውን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቅርቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 17 ጀምሮ ሲያካሄድ የነበረውን ጉባኤ አጠናቋል።
በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ በተሰጠ መግለጫም አንዳንድ ሃገራት ሃገራዊ የመልማት ፍላጎታችንን ለመግታት የሚያደረጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያ አንድነቷን ጠብቃ የቆየች መሆኑንም የዓለም ህዝብ ሊገነዘበው ይገባልም ብሏል።
የህዳሴ ግድቡ ሊጠናቀቅ ከዳር መድረሱን የገለጸው መግለጫው አሁንም ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርቧል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ 6ኛው ጠቅላላ ምርጫም በሠላም እንዲጠናቀቅም ሁሉን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል።
የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም በተሣካ መልኩ እንዲካሄድ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እንዲረባረቡም ጉባኤው ጥሪ አቅርቧል።