ኢትዮጵያ በአገራት መካከል ወዳጅነትና ትብብር ወሳኝ ናቸው አለች

ጥር 13/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ልማትን ለማረጋገጥ በአገራት መካከል ወዳጅነትና ትብብር ወሳኝ ምሰሶዎች ናቸው አለች።

በዓለም ዐቀፍ የልማት ተነሳሽነት ቡድን [the Group of Friends of Global Development Initiative] ምስረታ ላይ ኢትዮጵያ ለልማት ወሳኝ ምሰሶዎቹ ወዳጅነትና ትብብር ናቸው ስትል አፅንኦት መስጠቷን በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ለእኩልነትና አካታችነት መትጋትም እንደመንግሥታቱ ዘላቂ የልማት ግቦችና የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን መሰል የጋራ ግቦችን ለማሳካት መሳሪያ ናቸው ሲልም አክሏል።