ሩሲያና ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳዮችና ትብብራቸው ላይ ተወያዩ

ጥር 13/2014 (ዋልታ) በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አምባሳደር ትካቺንኮ ቪዚቮሎድ ኢጎሬቪች ጋር ተወያዩ።

አምባሳደር አለማየሁ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

በተያያዘም በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው የሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች ያለውን ትብብርን አጠናክሮ መቀጠል ስለሚቻልበት መንገድ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ሁለተኛው የሩሲያ አፍሪካ ፎረምን በተመለከተ የመከሩ ሲሆን ቀጣዩ የሁለትዮሽ የጋራ ስብሰባም በያዝነው የአውሮፓዊያኑ ዓመት እንደሚደረግ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡