ከ27 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት በአይነትና በገንዘብ ለመከላኪያ ሰራዊት ድጋፍ ተደረገ

ሐምሌ 27/2013 (ዋልታ) – የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችና አርሶ አደሮችም ከ27 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት በአይነት እና በገንዘብ ለመከላኪያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የክፍለ ከተማው አርሶ አደሮች ለሰራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት ለማሳያት 80 ሰንጋ በሬዎች፣ 66 በግ እና 70 ኩንታል የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶች ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስረከባቸውን የከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል፡፡