ሰኔ 02/2013 (ዋልታ) – በ1ወር ጊዜ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የቴሌ ብር አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ አደረገ፡፡
በዚህም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ በ69 ሚሊየን የገንዘብ ልውውጥ 360 ሚሊየን ብር ልውውጥ ተደርጓል፡፡
አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአቢሲኒያ ባንክ የተጀመረ ሲሆን በሌሎች ባንኮች እና የንግድ ተቋማት የአገልሎቱን ተደራሽነት ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ደንበኞች የቴሌ ብር አገልግሎትን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ማግኘት እንደሚችሉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
(በሳራ ስዩም)