ከሕዝብ የተደበቀ ድርድር አናደርግም – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 7/2014 (ዋልታ) ከሕወሓት ጋር ድርድር የሚለው ወሬ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ እና ከሕዝብ የተደበቀ ድርድር እንደማይደረግ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ድርድር ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያጣራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ፍላጎት ለጥይት የሚወጣውን ገንዘብ የመድኃኒት መግዣ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

በጦርነት የተገኘውን ድል በሰላም መድገም አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ለሰላም ዋጋ መክፈል እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል፡፡

አሸባሪው ሕወሓት ለትግራይ ሕዝብ ጥላቻ እና ልመና ብቻ ነው ያተረፈው ሲሉም አክለዋል፡፡