ከተማ አስተዳደሩ ለጽዳት ባለሙያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ መወሰኑ ተገለጸ

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – ከተማ አስተዳደሩ ለጽዳት ባለሙያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ መወሰኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የሌሊት ጨለማ፣ ብርድ፣ ዝናብ፣ ፀሃይ እና መጥፎ ሽታ ሳይሉ ለከተማችን ጽዳት ቀን ከሌሊት ለሚተጉትን የጽዳት ሰራተኞች ከተማ አስተዳደሩ ልዩ የምስጋና እና የምሳ መርሃግብር ማዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

እነኝህ የከተማዋ ያልተዘመረላቸው ጀግኖችን ማመስገን እና ክብር መስጠት ለሁላችንም ክብር ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፣ የከተማው አስተዳደሩም ስራቸውን በማክበር ለጽዳት ባለሙያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

የጽዳት ሰራተኞች 80 በመቶ እናቶች በመሆናቸው ይህ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጋላጭነታቸውን ይቀንሳል ብለዋል፡፡

ልፋታቸውን የሚመጥን ክብር እና ድጋፍ መስጠት ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን በማንሳትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል፡፡