ኅዳር 15/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬትጋር የስራ ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱ የሚዲያውን ስራ ለማዘመን አስፈላጊውን የቴክኖሎጂ አቅም በመጠቀም ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ኢንስቲትዩቱ በአቅም ግንባታ፣ በመረጃ አያያዝና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፍ እገዛ በማድረግ ከተቋሙ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ ንጉሤ መሸሻ (ዶ/ር) ስምምነቱ ለሚዲያው የለውጥ ስራዎች በቴክኖሎጂ ለመታገዝ ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸው በጋራ ለሀገራችን ትልቅ ስራ ለመስራት ያስችለናል ብለዋል።
በብርቱካን መልካሙ
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW