የሀረሪ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ


ሐምሌ 25/2013 (ዋልታ) –
የሀረሪ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የወረዳ ህዝብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ በተለይም የሀገርና ህዝብ ኩራት ለሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በፋይናንስ በአይነትና በሞራል እንዲሁም ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ከሰራዊቱ ጎን መቆም ይገባል ነው ያሉት፡፡

በእለቱም ከህዝብና መንግስት አካላት የተሰበሰበ የ10 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና 4 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ ሀገርን ለማዳን ለተሰለፉ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለክልል የጸጥታ አካላት የሚሆን ድጋፍ ወደ ስፍራው ለመላክና ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የክልሉ ህዝብና መንግስት ለሰራዊቱ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀው ለድጋፉ ለከተማና ገጠር ወረዳዎች፣ ለባለሃብቶች፣ ለወጣቶች፣ ለሀይማኖትና አባቶች የሀገር ሽማግሌዎችና አመራሮችን ማመስገናቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡